top of page

 

እ.አ.አ 27 ኦክተበር 2014 ላይ ሊሊ ቪ. ዊመንን (Lili V. Weemen ) ለሶመርሴት ዋርድ ቁጥር 14 ካውንስለርነት በሚደረገው የምርጫ ውድድር ይምረጧት።

ሊሊ የራሷ የሆነ አነስተኛ የንግድ ስራ ያላትና በሶስት አገራት ውስጥ በተለያዩ መንግስታዊ የኃላፊነት ደረጃዎች ላይ የሰራች፤ የአገር ውስጥና የዓለም አቀፋዊ የሥራ ልምድ ያላት ሴት ናት። በኦታዋ ማእከላዊ የከተማ ክፍል ውስጥ በሚከናወኑ ማኅበረሰባዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በመሳተፍ ረገድ ረጅም ታሪክ ያላት ሴት ከመሆኗም ባሻገር ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነችና ንቁ እንቅስቃሴ ያላት ከተማን ለመፍጠር በከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አዳዲስ ሐሳቦችን ማመንጨትና ማቅረብ ጠቃሚ ነው ብላ ታምናለች።

ሊሊ የመንገድ ግንባታ ሥራዎች በሚከናወኑበት ወቅት ሊፈጠሩ የሚችሉ ዋነኛ ችግሮችን ለመከላከል እና የመንገድ ለውጦችን ለማስቀረት ከተማችን የአውራ ጎዳናዎችን ንጽሕና ወደ መጠበቅና ሥራዎችን በተሻለ የቅንጅት ሥራ ወደመስራት መሠረታዊ መርህ ፊቷን መመለስ አላት ብላ ታምናለች። ቤት አልባነት ወይም በረንዳ አዳሪነት ካናዳን በመሰለ ሀብታም አገር ዋና ከተማ ውስጥ ማየት ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም። ለህጻናት፣ ለወጣቶች፣ ለአካል ጉዳተኞች እና ለአረጋዊያን ደኅንነትና ጤንነት በዘላቂነት ምቹ የሆነች ከተማ እንድትኖረን እንፈልጋለን። በከተማችን ማእከላዊ ክልል ውስጥ በመኪና መጠቀምን ለማስቀረት በመንገዶቻችን የሚንቀሳቀሱ ነጻ የከተማ ትራንስፖርት አውቶብሶች ሊኖሩን ይገባል። በሶመርሴት ዋርድ ውስጥ አዳዲስ የሥራ እድሎችን የሚፈጥር ለሥራና ለፈጠራ የተነቃቃ ታታሪ የንግድ ማኅበረሰብ እንዲኖረን ለማድረግ የግብር መጠንን መቀነስና የተለያዩ ማበረታቻዎችን ማድረግ አስፈላጊ ነው።

 

bottom of page